አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በሱዳን ከኢትዮጵያዉያን ማህበረሰብ አደረጃጀት መሪዎች ጋር ተወያዩ

አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ

ሰኔ 04/2013 (ዋልታ) – በሱዳን የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በሱዳን ከኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ አደረጃጀት መሪዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ እንዲሁም በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በፀረ -ሰላም ሀይሎች በተፈጠሩ የጸጥታ ችግሮች ምክንያት ከቤት ንብረታቸዉ የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም በመንግስት በኩል እየተደረገ ስላለዉ ጥረት እና በዉጭ ከሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ሊደረግ ስለሚችል ድጋፍ በካርቱም አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያዊያኑ በበኩላቸዉ፣ ወቅቱ በአንድነት መቆምን የሚጠይቅ እንደሆነ አንስተዉ፣ ለዜጎች አስፈላጊዉን እርዳታ ለማሰባሰብ እና በግላቸዉ አቅማቸዉ በፈቀደ ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁነታቸዉን ማረጋገጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።