ነሃሴ 20/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ጋር ተወያዩ።
የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።
ፕሬዝዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ከዚህ በኋላም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋቸዋል።
ሁለቱ መሪዎች በሁለትዮሽ የትብብር ግንኙነትና ዲፕሎማሲያዊ ግንኑታቸውን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን በቀጣናዊና አካባቢያዊ የፀጥታና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በትብብር እንደሚሰሩ ይታወቃል።
ሁለቱ አገሮች ከመንግስታዊ ግንኙነታቸው ባሻገር በህዝብ ለህዝብ ትስስር ጠንካራ መዳጅነት አላቸው።