ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ለስራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡትን የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲትን ዛሬ ረፋድ ላይ ተቀብለዋል

  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲትን አቀባበል ባደረጉበት ወቅት
ነሐሴ 1/2015 (አዲስ ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለአንድ ቀን የስራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡትን የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲትን ዛሬ ረፋድ ላይ ተቀብለዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በተካሄደው ስብሰባ ወቅት መሪዎቹ በሁለትዮሽ ጉዳዮች በንግድ፣ በመሰረተ ልማት ዝርጋታ እንዲሁም በቀጠናው ሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡