ጠ/ሚ ዐቢይ አዲስ ለተሾሙ የካቢኒ አባላት መልካም ምኞታቸውን ገለጹ

ጥቅምት 01/2014 (ዋልታ) በአዲሱ መንግሥት የተካተቱ ሚኒስትሮች እና ሚኒስትር ዴኤታዎች በዚህ ሳምንት በሚኖራቸው የሥራ ማስጀመሪያ ስልጠና ወቅት፣ በአገልጋይ መሪነት ልብ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው የዚህች ታላቅ ሀገር ዜጎች ተገቢ አገልግሎት ማግኘት ይገባቸዋል ብለዋል።