ጠ/ሚ ዐቢይ ከማልታ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

ሚያዝያ 30/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከማልታ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢያን ቦርግን ጋር ተወያዩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውይይታቸው ተከትሎ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ በንግድ እና በኢንቨስትመንት ግንኙነት ላይ፣ በተለይም የቱሪዝም ዘርፍን ለማሳደግ በተጠናከረ መልኩ ከማልታ ጋር ስለምንሠራበት ሁኔታ ተወያይተናል ብለዋል፡፡