ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ለአዲሱ የሱማልያ ፕሬዝደንት የደስታ መልዕክት አስተላለፉ

ግንቦት 10/2014 (ዋልታ) ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ አዲስ ለተመረጡት የጎረቤት ሱማልያ ፕሬዝደንት ሃሰን ሼክ ሞሐሙድ የደስታ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ፕሬዝዳንቷ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው ጠንካራ ግንኙነት ለሁለቱ ሀገር ሕዝቦች ጥቅም የበለጠ እንደሚያጠናክር ያላቸውን እምነት መግለፃቸውን ከፕሬዝደንት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።