ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከ6 ሺህ በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው እለት በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ6 ሺህ በላይ ተማሪዎች አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው በመደበኛ፣ በማታ እና በእረፍት ቀናት መርሀግብሮች ያሰለጠናቸውን 6ሺህ 263 ተማሪዎች ነው ያስመረቀው።

ከተመራቂዎቹ መካከል 6ቱ በዶክትሬት ዲግሪ፣ 514ቱ በማስተርስ ዲግሪ እንዲሁም 5ሺህ 626ቱ ደግሞ በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀዋል፡፡

ከተመራቂዎቹ መካከል 2ሺህ 144ቱ ሴቶች መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡