ሃገሪቱ የመጣው ለውጥ የጸና እንዲሆን የወጣቱ ሚና ከፍተኛ ነው – ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ

መጋቢት 17/2013 (ዋልታ) – በሃገሪቱ የመጣው ለውጥ የጸና እንዲሆን የወጣቱ ሚና ከፍተኛ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል፡፡

ምክትል ከንቲባዋ ከወጣቶች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

በሀገራችን እና በከተማችን ሰላም፣ እድገት እና ሁለንተናዊ ብልጽግና እንዲሰፍን ፈቃጅ እና ከልካይ እኛ ህዝቦቿ እንደሆንን አምነን በይቻላል መንፈስ በርትተን ልንሰራ ይገባል ሲሉ ነው በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት፡፡