ሆስፒታሉን በሰው ሀብትና በቴክኖሎጂ ለማደራጀት በርካታ ስራዎች መሰራታቸው ተገለጸ

የኢትዮጵያ ፖሊስ ሆስፒታል

የካቲት 3/2015 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ፖሊስ ሆስፒታልን በሰው ሀብትና በቴክኖሎጂ ለማደራጀት በርካታ ስራዎች መሰራታቸው ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ፖሊስ ሆስፒታል “ጤናችን በሆስፒታላችን ሰላምና ደህንነታችን በፖሊስ ሰራዊታችን” በሚል መሪ ቃል በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ 60ኛ ዓመት የአልማዝ እዩቤልዩ በዓሉን እያከበረ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በዝግጅቱ የተገኙ ሲሆን በሆስፒታሉ ተዟዙረው የሥራ ሂደቱን  በመጎብኘት የሲስተም ስራዎችን አስጀምረዋል።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የፊዴራል ፖሊስ አስተዳደርና ልማት ጠቅላይ መምሪያ ኃላፊ ነብዩ ዳኜ የፖሊስ የጤና አገልግሎት በጥራት ተደራሽ ለማድረግ በሰው ሀብትና በቴክኖሎጂ ለማደራጀት በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል።

በሌሎች የክልል ከተማ ዋና ዋና ቦታዎች ላይ ሆስፒታል ለመገንባት በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውንም አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ፖሎስ ሆስፒታል የጤና አገልግሎት ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ደረጄ ተካልኝ ሆስፒታሉ የፖሊስ ሰራዊቱን ጤና መጠበቅ የቻለ ነው ብለዋል።

በክብረ በዓሉ የፊዴራልና የክልል የፖሊስ ኮሚሽነሮች እንዲሁም የጤና መምሪያ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ሆስፒታሉ በ1955 የተመሰረተ ሲሆን ሀገርን በማገልገሉ ተሰማርተው ጉዳት የደረሰባቸውን የፖሊስ አባላት ሲያገለግል ላለፉት 60 ዓመታት ሲያገለግል እንደቆየ የሚታወቅ ነው።

በብሩክታይት አፈሩ