ኮሚሽኑ ሊመዘበር በሂደት ላይ የነበረ 998 ሚሊዮን ብር ማስቆም መቻሉን አስታወቀ

የካቲት 3/2015 (ዋልታ) ባለፉት ስደስት ወራት ሊመዘበር በሂደት ላይ የነበረ 998 ሚሊዮን ብር ማስቆም መቻሉን የፌዴራል ሥነምግባር እና ፀረሙስና ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ይህንን ያስታወቀው የ6 ወራት የስራ አፈጻጸሙን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ነው።

በዚህም በ6 ወሩ ሊመዘበር የነበረ 681 ሺሕ ካሬ ሜትር መሬት ማስቆም መቻሉንም አስታውቋል።

አስቸኳይ ሙስናን ከመከላከል አንጻር ከህዝቡ 1 ሺሕ 608 ጥቆማዎች መጥተዋል ያለው ኮሚሽኑ ከእነዚህ ጥቆማዎች መካከል 250 ተጨባጭ ችግር መሆኑ ተለይቶ ለምርመራ ለፌዴራል ፖሊስ እና ፍትህ ሚኒስቴር ተልኳል ብሏል።

ከመጡት ጥቆማዎች መካከል 40 በመቶው መሬት እና መሬት ነክ ጉዳዮች ስለመሆናቸውም ነው የተጠቆመው።

ኮሚሽኑ ያዘጋጀው ብሄራዊ የጸረ ሙስና ፖሊሲ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲጸድቅ ይቀርባልም ተብሏል።

በቃልኪዳን ሀሰን