የካቲት 05/2013 (ዋልታ) – የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልፈታ የሱፍ እንደገለፁት በከተማዋ ያሉ የገበያ ማዕከላትን በማስተሳሰር በተለይ ሸማቹ ማህበረሰብ ቀጥታ በተንቀሳቃሽ ስልክና የመገናኛ ዘዴዎች በመጠቀም መረጃዎችን በማግኘት ግብይት ማግኘት ያስችላል ብለዋል።
በተጨማሪም የምርት አቅርቦትና ፍላጎትን ለማወቅ፣ በምርቶች የተጋነነ ዋጋ ጭማሪን ለመለየት እና ሸማቹ ህብረተሰብ በየትኛው የገበያ ስፍራ በምን አይነት ምርት በምን ዋጋ እንደሚሸጥ ካለበት ሆኖ ለማወቅ እንደማያስችል ኃላፊው ገልጸዋል።
“www.aaminfo.gov.et “በሚል ይፋ የተደረገው የመረጃ ድህረገጽ ከ28 በላይ የገበያ ማዕከላት ጋር የተሳሰረ ሲሆን የከተማ አስተዳደር የግብይት ስርዓቱን ለማዘመን በትኩረት እየሰራ መሆኑን አቶ አብዱልፈታህ ተናግረዋል።
የመረጃ ሥርዓቱንም የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ እና ከአዲስ አበባ ከተማ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ኤጀንሲ ጋር በትብብር የተዘጋጀ ነው::
(ምንጭ:-የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪ)