ለመስቀል ደመራ በዓል የፅዳት ዘመቻ

ለመስቀል ደመራ በዓል የፅዳት ዘመቻ

መስከረም 14/2014 (ዋልታ) የመስቀል ደመራ በዓልን ምክንያት በማድረግ በእስጢፋኖስ ቤተክሪስቲያን እና በአካባቢው የፅዳት ዘመቻ ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ ደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ኤጀንሲ ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጋር በመቀናጀት በተካሄደው የፅዳት ንቅናቄ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች፣ የፅዳት አምባሳደሮች፣ ታዋቂ አርቲስቶች እና አትሌቶች እንዲሁም ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

በነገው ዕለትም ከተለያዩ የእምነት ተቋማት የተውጣጡ የሃይማኖት አባቶች፣ የአዲስ አበባ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባላት እና ተወካዮች፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረስብከት አድባራት እና ገዳማት አስተባባሪዎች፣ በጎፈቃደኛ ወጣቶች እና ነዋሪዎች የደመራ በዓል የሚከበርበትን መስቀል አደባባይ እና አካባቢውን የማስዳት እና የማሳመር መርኃግብር እንደሚካሄድ ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።