ለተፈናቀሉ ወገኖች የአረጋ ይርዳው (ዶ/ር) ድጋፍ

መስከረም 12/2014 (ዋልታ) የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አረጋ ይርዳው (ዶ/ር) እና ቤተሰቦቻቸው ከሰሜን ወሎ የተለያዩ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ።

የተደረገው ድጋፍ የተፈናቀሉ ወገኖችን  ፍላጎት መሰረት ያደረገ እንደሆነ የገለጹት አረጋ ይርዳው(ዶ/ር)፣ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ተጎጅዎቸን እንዲደግፍ ጠይቀዋል።

የተደረገው ድጋፍ የምግብ እህል፣ አልባሳት እንዲሁም የቤት ቁሳቁስን ያካተተ እንደሆነም ተገልጿል።

ድጋፉን የተረከቡት የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ወልደትንሳኤ መኮንን ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው፣ ከመንግስትና ከለጋሾች የሚመጣውን ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ለማዳረስ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በሳራ ስዩም