የብልጽግና ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ምክክር በሀገራዊ እና ቀጣናዊ አጀንዳዎች

መስከረም 12/2014 (ዋልታ) የብልጽግና ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በልዩ ልዩ ሀገራዊ እና ቀጣናዊ አጀንዳዎች ዙሪያ ምክክር ማድረጉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

ውይይት ከተደረገባቸው ጉዳዮች መካከል የሀገራችን ወቅታዊ የጸጥታና የደኅንነት ሁኔታ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች እንዲሁም ጂኦፖለቲካዊ ለውጦችን የተመለከቱ አጀንዳዎች እንደሚገኙበት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው አስታውቀዋል።

የሚታዩ ክፍተቶችን፣ ለውጥ የሚያስፈልጋቸው እና መሻሻል የሚገባቸውን ጉዳዮች በዝርዝር ገምግሞ በቀጣይ እንደ ሀገር መከናወን ስለሚገባቸው ተግባራት አቅጣጫዎችን እምዳስቀመጠም ገልጸዋል።

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!