ለአዲስ ተሿሚ አምባሳደሮች በሳይበር ደኅንነት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ

የካቲት 28/2014 (ዋልታ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ለአዲስ ተሿሚ አምባሳደሮች በሳይበር ደኅንነት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሰጠ፡፡

የአስተዳደሩ ዋና ዳይሬክተር ሹመቴ ግዛው (ዶ/ር) ስለሳይበር ደኅንነት ዓለም ዐቀፋዊ ሁኔታዎች፣ የዲጂታል ቴክኖሎጂ እድገት አወንታዊና አሉታዊ ተጽዕኖዎች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በኢመደአ የሳይበር ደኅንነት አስተዳደር ማዕከል ኃላፊ ፍጹም ወስኔ የሳይበር ደኅንነት ምንነትና ባህሪያት እንዲሁም ሊወሰዱ በሚገቡ የቅድመ ጥንቃቄ እርምጃዎች ዙሪያ ለአምባሳደሮቹ ገለጻ ማድረጋቸውን ከኢመደአ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዘመናዊ የዲፕሎማሲ ሥራን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ጋር በትብብር እየሠራ እንደሚገኝ የሚኒስቴሩ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ገልጸዋል፡፡