በነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ ተከስቶ የነበረው እሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ዋለ

ነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ 

የካቲት 28/2014 (ዋልታ) በነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

እንደኢፕድ ዘገባ የአደጋውን የጉዳት መጠን ለመቀነስና እሳቱን ሙሉ ለሙሉ ለማጥፋት የጋሞ ዞን፣ የአርባ ምንጭ ከተማ እና አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ፣ የጋሞ ዞን አካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ጽሕፈት ቤት ሰራተኞች እንዲሁም በርካታ ሚሊሻዎች እና ሬንጀሮች በጋራ በተደረገ ርብርብ እሳቱን በቁጥጥር ስር ለማዋል ተችሏል፡፡