ለ3.4 ሚሊየን ዜጎች የተፈጠረው የስራ ዕድል

መስከረም 13/2014 (ዋልታ) የስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን የጋራ መድረክ በባህርዳር እያካሔደ ነው።

የፌደራልና የክልል ስራ ዕድል ፈጠራ አካላት የሚሳተፉበት የጋራ መድረኩ የ2013 በጀት ዓመት አፈፃፀም፣ የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ እንዲሁም የኮቪድ-19 ተፅዕኖ የሚገመገምበት ነው ተብሏል።

በሀገሪቱ የሚስተዋለውና በገበያ ዘርፍ ከሚታዩ ችግሮች አንዱ የሆነውን የስራ ገበያው አካታች ባለመሆኑ ችግር ፈቺ የሆኑ ጥናቶች በመድረኩ እንደሚቀርብ ታውቋል።

በተጨማሪም የኮቪድ-19 በሽታ በጥቃቅን አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ላይ ያስከተለውን ተፅዕኖ በተመለከተም ጥናት ቀርቦ የመፍትሔ አቅጣጫዎች ይዳሰሱበታል ተብሏል።

ኮሚሽኑ በ2013 በጀት አመት 3 ሚሊየን የስራ ዕድሎችን ለመፍጠር አቅዶ 3.4 ሚሊየን የስራ ዕሎችን መፍጠሩንም አስታውቋል።

በ2014 የበጀት ዓመትም 3.1 የስራ ዕድሎችን ለመፍጠር ማቀዱን ገልጿል።

በሀገሪቱ ያለውን የስራአጥነት ችግር ለመቀነስ ቢያንስ በዓመት ለ3 ሚሊየን ዜጎች የስራ ዕድሎች መፈጠር እንዳለባቸው ይታመናል፡፡ የኢፌዴሪ ስራ ዕድል ፈጠራ ይህንን ግብ ከማሳካት አኳያ እስከ 2017 ዓ.ም 14 ሚሊየን የስራ ዕድሎች ለመፍጠር ማቀዱንም አስታውቋል።

በዙፋን አምባቸው