ግንቦት 5/2014 (ዋልታ) ሕወሓት የትግራይ ወጣቶችን ለጦርነት መመልመል መቀጠሉን የካናዳ ዊልፍሪድ ላውሪየር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፌሰር አን ፊትዝ-ጌራልድ ገለጹ።
ቡድኑ በአማራና አፋር ክልሎች ከሚገኙ አካባቢዎች ሙሉ ለሙሉ ለቆ አልወጣም ብለዋል።
የካናዳ ዊልፍሪድ ላውሪየር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሯ አን ፊትዝ-ጌራልድ (ፕ/ር) ሕወሓት በአሳዛኝ ሁኔታ የትግራይ ወጣቶችን ለጦርነት መመልመሉን ቀጥሏል፤ ይህም በዜጎች ላይ የጣለው እገዳና ግዴታ ነው ሲሉ በትዊተር ገጻቸው ያሰፈሩትን መረጃ ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል።
ቡድኑ አሁንም በአማራና አፋር ክልሎች የሚገኙ ቦታዎችን እንደያዘም አመልክተዋል።
የተናጠል ሰብአዊ ተኩስ አቁም ውሳኔ ያሳለፈው የኢትዮጵያ መንግሥት እንጂ ሕወሓት አይደለም ያሉት ፕሮፌሰሯ ተኩስ አቁሙ በሁለቱም ወገኖች ሊከበር ይገባል ብለዋል።
ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW