መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከፅንፈኛው ህወሓት የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ራሱን እንዲጠብቅ ጥሪ ቀረበ

ሐምሌ 30/2013 (ዋልታ) – መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ፅንፈኛው ህወሓት ከሚነዛው የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ራሱን እንዲጠብቅ የአማራ ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ግዛቸው ሙሉነህ ጥሪ አቀረቡ።
የጁንታው ሰርጐ ገቦች በተለያዩ ከተሞች ፎቶ በመነሳት ተቆጣጠርን እያሉ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ እያነዙ ነው ብለዋል፡፡
በአሁን ሰአት በዋግምራ ፣ በራያ እና በወልቃይት ግንባር ከፍተኛ ተጋድሎ መከለከያ ስራዊት የአማራ ልዩ ሐይል እና ሚለሻ እያደረገ ነው ብለዋል፡፡
አሸባሪው ቡድን በላሊበላ ሰርጐ መግባቱን የገለፁት ደይሬክተሩ አሁን ላይ በቊጥጥር ውስጥ ናቸው ብለዋል፡፡
በአማራ ክልል በአጠቃላይ ፅንፈኛው ቡድን በከፈተው ጦርነት ምክንያት በ 200 ሺህ በላይ ዜጐች ተፈናቅለዋል ብለዋል፡፡
የአማራ ክልል ልዩ ሀይል እና ሚለሻ ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በጋራ አሽባሪው ህወሓትን ለመቅበር ትልቅ ተጋድሎ እያደረጉ ነው ብለዋል፡፡
(በሜሮን መስፍን)