መርማሪ ቦርዱ ባካሄደው የመጀመሪያ ዙር የመስክ ምልከታ መግለጫ ሰጠ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ለማ ተሰማ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ባካሄደው የመጀመሪያ ዙር የመስክ ምልከታ በተመለከተ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መግለጫ ሰጥቷል፡፡

መርማሪ ቦርዱ በመጀመሪያ ዙር የመስክ ምልከታው በባህርዳር እና በጎንደር በሲቪል አየር መንገዶች ላይ የሕወሓት ጁንታ ቡድን ያደረሰውን የሮኬት ጥቃት በቦታው በመገኘት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ምልከታ ማድረጉን  የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም  መርማሪ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ለማ ተሰማ  በመግለጫው ገልጸዋል ፡፡

በሲቭል አየር መንገዶች ላይ ሮኬት ማስወንጨፍ በአለም አቀፍ ህግ እና ስምምነትቶች ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት መሆኑን ስለሚያስቀምጡ ጁንታ በአለም አቀፍ የወንጀል ህግ ተጠያቂ የሚሆን መሆኑንም ሰብሳቢው ገልጸዋል፡፡

በማይካድራ በተደረገው ጭፍጨፋ እጅግ ዘግናኝ መሆኑን በመግለጽ በአንድ መቃብር በርካታ አስክሬን መቀበራቸውንም ተጠቁሟል፡፡

ባህርዳ ምዕራብ እዝ ሆስፒታል እና በጎንር ዩኒቨርሲቴ ሆሰፒታ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ለምርከኞች እየተደረገ ያለውን ህክምና እና ሰብአዊ ድጋፍ የተመለከቱ ሲሆን አስፈላጊው እርዳታ እየተደረገ መሆኑንም ቦርዱ አስታውቋል፡፡

ጽንፈኛው ቡድን በሰሜን እዝ መከላከያ ሰራዊት ላይ በፈጸመው የክህደት ወንጀል የተለያዩ ክፍለ ጦሮች የተፈናቀሉ የሰራዊቱ ቤተሰቦች ተጠልው በሚገኙበት በጎንደር ህዳር 11 ትምህርት ቤት እና በአዘዞ ኮንዶሚኒየም አከባቢ በመገኘት ያሉበትን ሁኔታ እንዲሁም መንግስት እና የአካባቢው ማህበረሰብ እያደረገ ያለውን ድጋፍ መመልከታቸውንም ገልጸዋል፡፡

የጽንፈኛው ቡድን ያስታጠቃቸው ሀይሎች በሱዳን ተጠልለው ባሉ ወገኞች ላይ ጉዳት እንዳያደርሱም አስፈላጊው ጥበቃ እንዲደረግ ክትትል እየተደረገ እንደሚገኝም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርዱ አስታውቋል፡፡

 

(በሜሮን መስፍን)