ኢትዮጵያ የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪውን ለመደገፍ የሚያስችል ስምምነት ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር ተፈራረመች

 የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (UNIDO) እና የጀርመን ተራድኦ ድርጅ(GIZ) የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪውን ለመደገፍና ለማሳደግና የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ፡፡

የሶስትዮሽ ስምምነቱን በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአግሮ ፕሮሰሲንግ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ተካ ገብረየሱስ፣ የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ተወካይ እና የቀጠናው ዳይሬክተር ኦሬሊያ ፓትሪዚያ ካላብሮ አካሂደዋል፡፡

ስምምነቱም በኢትዮጵያ የሚገኙ የቻይና ፋብሪካዎችንና የሀገር ውስጥ የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪዎችን አቅም በመገንባት ማህበራዊና አካባቢያዊ ኃላፊነታቸውን የሚወጡና ዘላቂና ቀጣይነት ያለው የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ መገንባት መሆኑ ተነግሯል፡፡

የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ዘርፉን ለማሳደግ የሚካሄደው ሁለንተናዊ ድጋፍ ከቻይና መንግስት በሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ በተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት አስተባባሪነት የሚከናወን መሆኑን ዳይሬክተሯ ኦሬሊያ ፓትሪዚያ ካላብሮ ገልፀዋል፡፡

የቻይና መንግስትና የተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ሁለንተናዊ  ድጋፍ ያመሰገኑት ሚኒስቴር ዴኤታው ወደፊትም አብሮ ለመስራት የመንግስትን ዝግጁነት መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።