መስከረም 22 እና 23 የሚከበረው የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል

መስከረም 19/2014 (ዋልታ) የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መስከረም 22 እና 23 እንደሚከበር የበዓሉ አስተባባሪ ኮሚቴ አስታወቀ።

በየዓመቱ በመስከረም ወር ሁለት ጊዜ የሚከበረው የዘንድሮ የኢሬቻ መልካ በዓል መስከረም 22 እና 23 እንደሚከበር የበዓሉ አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ ከበደ ዴሲሳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል መስከረም 22 የሚከበር ሲሆን፣ የሆራ አርሰዲ ኢሬቻ በዓል ደግሞ መስከረም 23/ 2014 ዓ.ም በቢሾፍቱ ይከበራል ብለዋል።

የኢሬቻ በዓል በርካታ ህዝብ የሚታደምበት ክብረ በዓል እንደሆነና የዘንድሮ በዓል በሰላም እና በአብሮነት በደመቀ መልኩ እንዲከበር አስፈላጊ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውንም ገልጸዋል።

በደረሰ አማረ