መቀሌ ከተማ የቴሌኮም አገልግሎት ማግኘቷ ተገለጸ

ፍሬሕይወት ታምሩ

ታኅሣሥ 19/2015 (ዋልታ) በዛሬው እለት መቀሌ ከተማ የቴሌኮም አገልግሎት ማግኘቱን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ አስታወቁ።

የመጀመሪያው የስልክ ጥሪ በመቀሌ እንደተካሄደም ነው ኢትዮ ቴሌኮም ያስታወቀው።

ከሰላም ስምምነቱ ማግስት በተሰራ ስራ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል 27 ከተሞች የቴሌኮም አገልግሎት ማግኘት መቻሉንም ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል።

የባንክ ብሎም የቴሌኮም ጥገና በማድረግ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑንና 981 የኢትዮ ቴሌኮም ፋይበር ጥገና መደረጉን ተቋሙ አመልክቷል።

በክልሉ 61 ባንኮችም አገልግሎት መጀመሩን ነው ኢትዮ ቴሌኮም ያስታወቀው።

በሱራፌል መንግስቴ