ብራዚላዊው የእግር ኳስ ንጉስ ተብሎ የሚጠራው ፔሌ ህይወቱ አለፈ

ፔሌ

ታኅሣሥ 21/2015 (ዋልታ) ብራዚላዊው የእግር ኳስ ንጉስ ተብሎ የሚጠራው ፔሌ ህይወቱ አለፈ።

የሦስት ጊዜ ዓለም ዋንጫ አሸናፊው ፔል በ82 ዓመቱ በአንጀት ካንሰር ህመም ህይወቱ ማለፉ ነው የተሰማው።

ፔል በዓለም ዋንጫ በመሳተፍ በዕድሜ ትንሹ ተጨዋች ሲሆን 1958፣ 1962 እና 1970 ከብራዚል ብሔራዊ ቡድን ጋር የዓለም ዋንጫን ማሳካት ችሏል።

በሚኪያስ ምትኩ