መጪው ሀገር አቀፍ ምክክር በአጨቃጫቂ ጉዳዮች ላይ መግባባትን ለማምጣት በምናደርገው የጋራ ጥረት ወሳኝ ምዕራፍ እንደሚሆን አምናለሁ – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

መስከረም 22/2016 (አዲስ ዋልታ) መጪው ሀገር አቀፍ ምክክር በአጨቃጫቂ ጉዳዮች ላይ መግባባትን ለማምጣት በምናደርገው የጋራ ጥረት ወሳኝ ምዕራፍ እንደሚሆን አምናለሁ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለፁ፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በዛሬው ዕለት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ለከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የሥራ ሂደቱን ሪፖርት አቅርቧል።

በዚህም የተቋማት ግንባታ፣ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ፣ የውይይት ሂደት መቅረጽ፣ የውይይት ተሳታፊዎችን መለየት እንዲሁም ቀጣይ የሚሠሩ ተግባራትን እና ለተሳካ የውይይት ሂደት መቀረፍ ያለባቸውን ችግሮች ጨምሮ ኮሚሽኑ እስካሁን ያከናወናቸውን ተግባራት ሂደት ማቅረቡ ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት ዛሬ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አባላትን አግኝቼ ሥራዎቻቸው ስላሉበት ደረጃ ተወያይተናል ብለዋል።

በዚህም መጪው ሀገር አቀፍ ምክክር በአጨቃጫቂ ጉዳዮች ላይ መግባባትን ለማምጣት በምናደርገው የጋራ ጥረት ወሳኝ ምዕራፍ እንደሚሆን አምናለሁ ሲሉ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለፁት፡፡