ሙስናን ለመዋጋት ከህዝባዊ ድርጅቶች ጋር ተባብሮ መስራት  የጎላ ሚና እንዳለው ተገለጸ

ሚያዝያ 14/2013 (ዋልታ) – ሙስናን ለመዋጋት ከህዝባዊ ድርጅቶች ጋር ተባብሮ መስራት  የጎላ ሚና እንዳለው ተገለጸ፡፡

የፌዴራል የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን በህዝባዊ ድርጅቶች የተቀናጀ ስራ ሙስናን እንዴት መከላከል ይቻላል? በሚል ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

በውይይቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፌዴራል የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ወዶ አጦ ሙስናና ብልሹ አሰራርን መፍታት የሚቻለው በአንድ ተቋም ብቻ እንዳልሆነ ገልጸው፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ያለውን ሙስናን የመዋጋት ተግባር ከህዝባዊ ድርጅቶች ጋር ተባብሮ መስራት  የጎላ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።

ተቋሙም ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የ10 አመት እቅድ አውጥቶ ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

በውይይቱ ላይ አዋጅ ቁጥር 1236/2013 የፌዴራል የሥነ ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ እንደገና ለማሻሻል በወጣ አዋጅ ላይ ምክክር እየተደረገ ይገኛል።

(በሱራፌል መንግስቴ)