መጋቢት 3/2013 (ዋልታ) – ሀሰተኛ ደረሰኝ በማሰራጨት ሲያጭበረብሩ የነበሩ 42 ድርጅቶች መለየታቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴሩ ድርጅቶቹ ባለፉት ሰባት ወራት በሃሰተኛ ደረሰኝ ሲያጭበረብሩ የነበሩና በጥናት የተለዩ መሆናቸውንም አስታውቋል፡፡
ከተዘረዘሩት ህገ ወጥ ድርጅቶች ግብይት የፈፀሙ አካላት ኦዲት እንደሚደረጉ በመጥቀስ፣ ድርጅቶች በቀጣይ ከተዘረዘሩት ድርጅቶች ግብይት እንዳይፈጽሙም መልዕክት አስተላልፏል፡፡
የድርጅቶቹ ድርጊት ሃገር ማግኘት የሚገባትን ገቢ ከመሳጣቱም በላይ የንግድ ስርዓቱን በማዛበት ህጋዊ ነጋዴዎችን ከገበያ እንደሚያስወጡም ገልጿል፡፡