ሚኒስትሩ የዲያስፖራ አባላት ጋር ተወያዩ

ሚያዝያ 29/2014 (ዋልታ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን “ከኢድ እስከ ኢድ ወደ አገር ቤት” ጥሪ ተቀብለው ከመጡ ዲያስፖራ አባላት ጋር ተወያዩ፡፡

ሚኒስትሩ ያነጋገሯቸው የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማኅበረሰብ አባላት ከዩናይትድ ኪንግደም የመጡ መሆናቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።