ሜጀር ጄነራል ቹሃድ ዋሃሪ በደቡብ ሱዳን የተሰማራውን 14ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ ጎበኙ

በተባበሩት መንግስታት በደቡብ ሱዳን የዩናሚስ ምክትል ሃይል አዛዥ ሜጀር ጄነራል ቹሃድ ዋሃሪ በ14ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ የስራ ጉብኝት አደረጉ ፡፡

የ14ኛ ሞተራይዝድ ዋና አዛዥ ኮ/ል መለስ መንግስቴ አቅራቢነት ፣ በግዳጅ አፈፃፀም እና ግዳጅን ለመፈፀም መሰናክል ስለሆኑ ችግሮች ሻለቃው ቀጣናውን ከተረከበ ጀምሮ የተከናወኑ ስራዎች አፈፃፀም ላይ ውይይት ተደርጓል ፡፡

በተለይም በሃገራችን የሰሜኑ ክፍል እየተወሰደ ባለው ህግ ማስከበር ዘመቻ በሻለቃው ዋና አዛዥ ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል ፡፡

ሜጀር ጀነራል ቹሃድ በበኩላቸው ፣ ሻለቃው ቀጠናውን ከተረከበ ጊዜ ጀምሮ የደቡብ ሱዳን የሰላም ሁኔታ እየተሻሻለ መምጣቱን ገልፀው ውጤታማ ስራ በማከናወናችሁ እንኮራባቹሃለን ብለዋል ፡፡

በወቅቱ በኢትዮጵያ የተፈጠረውን ጉዳይ ሲከታተሉት መቆየታቸውን እና በተደረገላቸው ገለፃ ሁኔታውን በአግባቡ መረዳታቸውን ገልፀው ፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ ሰላምና ልማትን ተመኝተዋል።

(ምንጭ ፡- የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት )