ምክር ቤቱ 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ ልዩ ስብሰባውን እያካሄደ ነው

ሰኔ 28/2013 (ዋልታ) – የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ ልዩ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል፡፡

ምክር ቤቱ ልዩ ስብሰባውን የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት እያካሄደ የሚገኝ ሲሆን፣ በልዩ ስብሰባው የፌዴራል መንግስትን የ2014 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ላይ ተወያይቶ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ ስብሰባ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ የአለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡