ምክትል ከነቲባዋ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ እየተገነባ ያለውን የገበያ ማዕከል ጎበኙ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ በአንድ ቢሊየን ብር ወጪ እየተገነባ ያለውን የአትክልት ተራ የገበያ ማዕከል የግንባታ ሥራን ትላንት ምሽት ጎብኝተዋል።

ይህ በሁለት ምዕራፍ ተከፍሎ እተየገነባ ያለው የአትክልት ተራ የገበያ ማዕከል በመጀመሪያው ምዕራፍ የሚገነቡት የመገበያያ ሼዶች ከ70 በመቶ በላይ መጠናቀቃቸውን የገመገሙ መሆኑን ወ/ሮ አዳነች በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው አስታውቀዋል።

በመጀመሪያው ምዕራፍ ከሚገነቡት 14 ሼዶች ውስጥ 588ቱ የመገበያያ ሱቆች ያሉት መሆኑ ተገልጿል።

ምክትል ከንቲባዋ ይህንን ሥራ በሦስት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ሌት ተቀን ለሠሩት የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን እና ለአሠሪው የአዲስ አበባ ኮንስትራክሽን ቢሮ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።