ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከእንግሊዝ የአፍሪካ ቀንድ እና ቀይ ባህር ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ

ነሐሴ 11/2014 (ዋልታ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከእንግሊዝ የአፍሪካ ቀንድ እና ቀይ ባህር ልዩ መልዕክተኛ ሳራ ሞንትጎመሪ ጋር ተወያዩ።

በውይይቱም እንግሊዝ ከኢትዮጵያ ጋር ስላላት የረጅም ጊዜ ወዳጅነት አስታውሰው በእንግሊዝ መንግስት በኩል እየቀረበ ላለው ዘርፈ ብዙ ድጋፍም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በኢትዮጵያ የሰሜኑ ክፍል የተፈጠረውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት መንግስት ቁርጠኛ መሆኑን ጠቅሰው ችግሩን ለመፍታት በመንግስት በኩል እየተወሰዱ ስላሉ ዝርዝር ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ልዩ መልዕክተኛዋም በበኩላቸው በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው የረጅም ጊዜ ወዳጅነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የድርሻቸውን እንደሚወጡ ገልጸው የሰላም ሂደቱንም ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸው ጠቁመዋል፡፡