ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጃፓን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እና የጃፓኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃያሺ ዮሺማሳ

ሐምሌ 27/2015 (ዋልታ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከጃፓን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃያሺ ዮሺማሳ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ተወያዩ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጃፓኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በሁለትዮሽ፣ ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ተናግረዋል።

ጃፓን ከኢትዮጵያ ጋር ታሪካዊ ወዳጅነት ያላት ሀገር መሆኗን የጠቀሱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ወቅቱ በሚጠይቀው መልክ ማሳደግ ይፈልጋል ብለዋል።

የጃፓን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀያሺ ዮሺማስ በበኩላቸው የኢትዮጵያ መንግስት በፕሪቶሪያ ለተደረሰው የሰላም ስምምነት እውቅና የሰጡ ሲሆን ጃፓን ለስምምነቱ ትግበራ ድጋፍ እንደምታደርግ አረጋግጠዋል።

ጃፓን ከኢትዮጵያ ጋር በኢኮኖሚው መስክ በትብብር ለመስራት ያላትን ፍላጎትም ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ከሩስያና ዩክሬን ጦርነት ጋር ተያይዞ በአፍሪካ የምግብ ደህንነት ጉዳይ ጥያቄ ወስጥ መግባቱን ተወያይተናል ያሉት የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አገራቸው ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗንም አመልክተዋል፡፡

በቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ አሳሳቢ ጉዳዮችን መፍታት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይም መምከራቸውም ተገልጿል፡፡

 

በመስከረም ቸርነት