ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከአፍሪካ ብሔራዊ የኦሎምፒክ ኮሚቴዎች ማኅበር ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የአፍሪካ ብሔራዊ የኦሎምፒክ ኮሚቴዎች ማኅበር ፕሬዚዳንት ሙስጠፋ ቤራፍን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ፕሬዝዳንቱ መጪው እሁድ በሚካሄደው የአፍሪካ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
በዕለቱ አቶ ደመቀ በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ስታዲየሞች እና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን መገንባትን በመጥቀስ የኢትዮጵያ ክልል ከተሞች ዓለም አቀፍ የስፖርት ውድድሮችን ለማስተናገድ አቅም እንዳላቸው ለፕሬዘዳንቱ ገለጻ አድርገዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ ሚንስተሩ ላደረጉላቸው አቀባበል አመሰግነው በኢትዮጵያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርበት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡