ም/ጠ/ሚኒስትሩ ከደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ጋር ተወያዩ

ታኅሣሥ 7/2014 (ዋልታ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ጋር ተወያዩ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደመቀ ዛሬ በጁባ የአንድ ቀን ጉብኝት አድርገዋል።
በጉብኝታቸው ከአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ጋር በሁለቱ አገራት ግንኙነት ዙሪያ መወያየታቸውን ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው በኩል ባስተላለፉት መልዕክት የገለጹት።