ሞሮኮ ከእስራኤል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለመጀመር ከተስማሙ የአረብ አገራት ዝርዝር ውስጥ ተካታለች።
በአሜሪካ አደራዳሪነት የተደረሰውን ስምምነት ፕሬዝደንት ትራምፕ በትዊተር ገጻቸው ይፋ አድርገዋል።
ሞሮኮ ከእስራኤል ጋር ከስምምነት መድረሷን ተከትሎ በዌስተርን ሳሃራ ግዛት ለምታነሳው የይገባኛል ጥያቄ አሜሪካ እውቅና ለመስጠት ተስማምታለች።
ሞሮኮ ከነሐሴ ወር ወዲህ ከእስራሴል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማሻሻል ከስምምነት የደረሰች አራተኛዋ አገር ሆናለች።
በቅርቡ የትራምፕ አስተዳደር ሱዳን፣ ዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ እና ባህሬን ከእስራኤል ጋር ሰላም እንዲያወርዱ ማደራደሩ ይታወሳል።
ከዚህ ቀደም ከእስራኤል ጋር የሰላም ስምምነት የፈረሙት ግብጽ እና ጆርዳን ሲደመሩ፤ ከአረብ ሊግ አባል አገራት ከእስራኤል ጋር የሰላም ስምምነት የደረሱት አገራት ቁጥር ወደ ስድስት ከፍ ይላል ሲል ቢቢሲ በድረ ገፁ ዘግቧል፡፡