ሩሲያ የድል ቀኗን እያከበረች ነው

ግንቦት 1/2015 (ዋልታ) ሩሲያ የቀድሞ ሶቪየት ህብረት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ናዚ ጀርመንን ያሸነፈችበትን 78ኛ ዓመት የድል ቀን በሞስኮ እያከበረች ነው።

ፕሬዝዳንት ቭላዲሜር ፑቲን በበዓሉ ላይ ባደረጉት ንግግር ዓለም በወሳኝ የለውጥ ጊዜ ላይ መሆኗን ጠቅሰው ምዕራባዊያን በሩሲያ ላይ በይፋ ጦርነት እንደከፈቱባት ገልጸዋል።

ሩሲያ ከዩክሬን ጋር እያደረገች ያለችው ጦርነት የጸረ ናዚዝም እሳቤ እና ሉዓላዊነትን የማስከበር ትግል መሆኑንም በንግግራቸው አመልክተዋል።

በሥነ ሥርዓቱ ላይ በእግረኛ ወታደሮች፣ ታንኮች እና ሚሳኤሎች የታጀበ የወታደራዊ ሰልፍ ትርዒት ተካሂዷል፡፡

በምዕራብ ግንባር የናዚ ጦር ሶቪየት ህብረትን በወረረበት ወቅት ከየሶቭየቱ ቀዩ ጦር ከባድ ምት ደርሶበት የተፍረከረከው እና ከ91 ሺሕ በላይ ተዋጊ የተማረከበት ስታንግራድ በተባለ ቦታ ነበር፡፡

የናዚ ሽንፈት የመጀመሪያው መጨረሻ የተባለለት ይህ ጦርነት ለሶቭየቶች ጣፋጭ ድል በመሆኑ ሩሲያ በየዓመቱ በድምቀት ትዘክረዋለች፡፡