የካቲት 12/ 2013 (ዋልታ) – የስዊዲን መንግስት ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ተፈናቅለው በአማራ ክልል አዊ ዞን ቻግኒ ከተማ ለሚገኙ ዜጎች 6 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት የሰብአዊ ድጋፍ ማድረጉን በኢትዮጵያ የስዊዲን ኤምባሲ አስታወቀ።
በኢትዮጵያ የስዊዲን አምባሳደር ሃንስ ሄነሪክ ሉንድኩዊስት የተመራ ልዑክ በቻግኒ ከተማ የሚገኙ የመተከል ዞን ተፈናቃዮችን ጎብኝቷል።
ልዑኩ በነበረው ቆይታ ተፈናቃዮችን የጎበኘ ሲሆን ከአማራ ክልል ርእሰ መስትዳደር አቶ አገኘው ተሻገርና ከክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር መወያየቱን ኢዜአ ከኤምባሲው ያገኘው መረጃ ያሳያል።
የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመደገፍም የስዊድን መንግስት በዩኒሴፍ በኩል 6 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ የሰብአዊ ድጋፍ ማድረጉ ተገልጿል።