ሽብርተኝነትን በጋራ መከላከል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር እየተደረገ ነው

ሰኔ 23/2013 (ዋልታ) – በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጽሕፈት ቤት ሽብርተኝነትን በጋራ መከላከል ላይ ያተኮረ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

በሰላም ሚኒስቴር የሕግ ማስከበር ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ፍሬዓለም ሽባባው በውይይቱ ላይ በድርጅቱ የ72 ዓመታት የቋሚ አባልነት ታሪክ ያላት ኢትዮጵያ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት እያከናወነች ያለውን ተግባር አብራርተዋል።
ኢትዮጵያ ሽብርተኝነትን በመዋጋት ትልቅ አጋርነት ያላት ሀገር መሆኗንም ገልጸዋል፡፡
አሁን በተደረሰበት የቴክኖሎጂ ዘመን ሀገራት ከሽብርተኝነት ጋር የተያያዙ አዳዲስ ፈተናዎችን በምን መልኩ ሊፋለሙ ይገባል በሚል ሐሳብ ዙሪያ 200 የዓለም ሀገራት እና የፀረ ሽብር ሥራን የሚያከናወኑ ተቋማት ተሳትፈዋል፡፡
በውይይቱ ሽብረተኝነትን ለመከላከል ሀገራት በጋራ አብረው መቆም እንደሚገባቸው መነገሩን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡