ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በጋምቤላ ያስገነቡትን ት/ቤት አስመረቁ

 

የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት በጋምቤላ ከተማ አስተዳደር 05 ቀበሌ ያስገነባውን ጋምቤላ ብርሀን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በዛሬው እለት አስመርቋል፡፡

ለግንባታው 13.8 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገለት ሲሆን ትምህርት ቤቱ በሁለት ፈረቃ 1ሺህ 800 ተማሪዎችን የመቀበል አቅም እንዳለው ጽ/ቤቱ አስታውቋል፡፡