ቀዳማዊት እመቤቷ ለሁለተኛው ዙር ትምህርት ቤት ግንባታ መሰረት ድንጋይ አስቀመጡ

ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው ለሁለተኛው ዙር ትምህርት ቤት ግንባታ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።

የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት በመጀመሪያ ዙር በሁሉም ክልሎች ያስገነባቸዉን 20 ሁለተኛ ደረጃ ትምርህርት ቤቶችን በመመረቅ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የመደመር መጽሐፍ ገቢ ትምህርት ቤቶች በሌሉባቸው አካባቢዎች ት/ቤቶችን የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት እንዲገነባ ማስረከባቸው አይዘነጋም።

በመሆኑም ክልሎች መጽሀፉን ሽጠዉ ካስገቡት ገንዘብ ትምህርት ቤቶቹ እንደሚገነቡ ቃል በተገባላቸዉ መሰረት በኦ/ብ/ክ/መ በምእራብ አርሲ ዞን ሲራሮ ወረዳ ሮጲ ከተማ ለሚገነባዉ ኢፋ ሮጲ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዛሬ የሁለተኛዉ ዙር ትምህርት ቤት ግንባታ የመጀመሪያዉ የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል፡፡

የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ ስነ ስርአቱን ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸዉ እና የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልሽ ማከናቻን ከቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡