ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ሆነ

ሰኔ 24/2014 (ዋልታ) አንጋፋው የስፖርት ክለብ ቅዱስ ጊዮርጊስ የዘንድሮው የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ ሆኗል።

በ30ኛ ሳምንት የፕሪምየር ሊጉ መርኃ-ግብር አዲስ አበባ ከተማን የገጠሙት ፈረሰኞቹ 4 ለ 0 አሸንፈው ለ15ኛ ጊዜ የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ አንስተዋል፡፡

በተመሳሳይ ሰዓት በተከናወነ ጨዋታ ፋሲል ከነማ በድሬዳዋ ከተማ ሦስት ለሁለት ተሸንፏል፡፡

ከሊጉ አዲስ አበባ ከተማ መሸነፉን ተከትሎ መውረዱን አረጋግጧል፡፡