በሀረሪ ክልል እየተከናወኑ የሚገኙ የፀጥታ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ – ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ

ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ

መስከረም 10/2015 (ዋልታ) በሀረሪ ክልል እየተከናወኑ የሚገኙ የፀጥታ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለጹ፡፡

የሀረሪ ክልል የፀጥታው ምክር ቤት በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ ፀጥታ ስራዎች ዙሪያ ውይይት ያደረገ ሲሆን የክልሉን ሰላምና ፀጥታን ለማጎልበት የተከናወኑ ተግባራትን በሚመለከት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ እንዳሉት በክልሉ እየተስተዋለ የሚገኘው አንፃራዊ ሰላም ተጠናክሮ እንዲቀጥል በቅንጅት ይሰራል።

በተለይም በክልሉ የሚከበሩ ህዝባዊና ሃይማኖታዊ በዓላት በሰላም እንዳጠናቀቁ ልዩ ትኩረት ይሰጣል ነው ያሉት።

ከዚህ በተጨማሪም በኮንትሮባንድ፣ ህገወጥ የጦር መሳሪያና ህገወጥ የሰዎች ዝውውር እንዲሁም በአደንዛዥ ዕፅ ቁጥጥር ላይ የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል።

የክልሉ ሰላምና ፀጥታ እንዲጠናከርም በተለይ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የኦሮሚያ ልዩ ኃይልና የክልሉ የፀጥታ ኃይሎች በቅንጅት እየሰሩ ስለመሆኑ ተነስቷል።

ተስፋዬ ኃይሉ (ከሀረር ቅርንጫፍ)

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW