የዓለም ባንክ በተለያዩ መስኮች የጀመራቸውን የትብብርና ድጋፍ ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ

መስከረም 10/2015 (ዋልታ) የዓለም ባንክ በተለያዩ መስኮች ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የጀመራቸውን የትብብርና ድጋፍ ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ፡፡

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) የዓለም ባንክ ተወካዮችን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ እየተተገበረ ባለው የአካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለዉጥ መቋቋምና መከላከል ላይ እየተሰራ ያለዉን ስራና ከብሄራዊ አካዉንት መረጃ አያያዝና የተፈጥሮ ሃብትን በሀገራዊ ምርት እድገት ላይ ያለዉን ድርሻ በተመለከተ እንዲሁም መረጃ አያያዝን እና መረጃን በአግባቡ መጠቀምን በተመለከተ ሰፊ ዉይይት ተደርጓል፡፡

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ የዓለም ባንክ የሚደርገዉን ድጋፍ የኢትዮጵያ መንግስት በ10 ዓመቱ የልማት እቅድ ዉስጥ ቅድሚያ እና ትኩረት በሰጣቸዉ መስኮች ላይ ማተኮር እንዳለበት ገልጸዋል፡፡

የዓለም ባንክ በተለያዩ መስኮች ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የጀመራቸዉን የትብብርና የድጋፍ ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል እንዲሁም ሀገሪቱ በጀመረቻቸዉና ቅድሚያ በምትሰጣቸዉ መስኮች ላይ ድጋፉን እንደሚያጠናክር ማሳወቁን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW