በሀገሪቱ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ወደ 31.7 በመቶ ከፍ አለ

ኅዳር 1/2015 (ዋልታ) የባለፈው ጥቅምት ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 31 ነጥብ 7 በመቶ ሆኖ መመዝገቡን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

የመስከረም ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 30 ነጥብ 7 በመቶ የነበረ ሲሆን በጥቅምት ወር አንድ በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በወርሃዊ ሪፖርቱ እንዳመለከተው የአጠቃላይ ዋጋ ግሽበት መጠን መጨመር ዋና ምክንያት በነዳጅ ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ባለፉት 5 ወራት የምግብ ዋጋ ግሽበት መጠን በተከታታይ ቅናሽ አሳይቷል ያለው አገልግሎቱ ምግብ ነክ ያልሆኑት የዋጋ ግሽበት መጠን በጥቅምት ወር 2015 ዓ.ም መጠነኛ ጭማሪ ማሳየቱን አመላክቷል፡፡

የዋጋ ግሽበት በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ባደጉ አገራትም ጭምር ፈተና ሆኗ መቀጠሉን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት መረጃ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW