በመስቀል አደባባይ በተደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት 10 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡ ተገለፀ

ጥር 4/2014 (ዋልታ) “ለኢትዮጵያ ምልጃና የአምልኮ ጊዜ” በሚል በመስቀል አደባባይ በጦርነቱ ለተፈናቀሉ ወገኖች በተደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ 10 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡ ተገለጸ፡፡

በዘፀዐት አፖስቶሊክ ሪፎርሜሽን ቤተክርስቲያን አዘጋጅነት በተካሄደው መርሃ ግብር ድጋፉ መሰብሰቡን የቤተክርስቲያኗ መሪ ሐዋሪያ ዮሐንስ ግርማ ተናግረዋል።

የ10 ሚሊዮን ብር ድጋፉን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ ጥራቱ በየነ መረከቡን ከከተማ አስተዳደሩ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል::