በመዲናዋ በአንድ ግለሰብ የሸቀጣ ሸቀጥ መደብር ውስጥ ተቀጣጣይ ቁሳቁስና ኬሚካሎች ተያዙ

ኅዳር 12/2014(ዋልታ) በአዲስ አበባ በአንድ ግለሰብ የሸቀጣ ሸቀጥ መደብር ውስጥ ተቀጣጣይ ቁሳቁሶችና ኬሚካሎች መያዛቸው ተገለፀ፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊሰ ኮሚሽን ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ በአሁኑ ወቅትነዋሪነቱን በሳውዲ አረቢያ ያደረገ አቶ መሀመድ ሀሰን የተባለ ግለሰብ ተቀጣጣይ ቁሳቁሶችናኬሚካሎችን ሸቀጣ ሸቀጦችን እንደሽፋን ተጠቅሞ በመደብሩ ውስጥ ደብቆ የተገኘ መሆኑን ጠቅሷል፡፡

ግለሰቡ ከሀገራዊ ለውጡ በፊት ለሽብርተኛው ህዋሃት በርካታ ገንዘብ በመላክ ከጁንታው አመራሮች ጋርየጥቅም ትስስር በመፍጠር “ተቀጣጣይ ማቴሪያሎችና ኬሚካሎች ችርቻሮ ንግድ”በሚል ፍቃድ አውጥቶሲንቀሳቀስ እንደነበር ያስታወቀው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፤ ግለሰቡ ይሄንን የንግድ ፈቃዱን ከሀገራዊለውጡ በኋላ ደግሞ “የሸቀጣ ሸቀጥ ችርቻሮ ንግድ” በሚል ቀይሮ ሲንቀሳቀስ የቆየ መሆኑን አመልክቷል፡፡

የደህንነትና ፀጥታ አካላት ጉዳዩን በጋር ሲከታተሉ ከቆዩ በኋላ የግለሰቡ የሸቀጣ ሸቀጥ ችርቻሮ ንግድመደብር በሚገኝበት በአዲስ አበባ ከተማ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ቀጠና 5 ተብሎበሚጠራው አካባቢ በተደረገ ፍተሻ በርካታ ተቀጣጣይ ቁሳቁሶችና ኬሚካሎች መገኘታቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

በአሁኑ ወቅትም መደብሩ እንዲታሸግ ተደርጎ በፖሊስ አባላት እንዲጠበቅ መደረጉን የአዲስአበባ ፖሊስ ኮሚሽን በመግለጫው ጠቁሟል፡፡

በተያያዘ በአንድ ግለሰብ የቁጠባ ሂሳብ ደብተር ውስጥ ከነበረ 40 ሚሊዮን ብር 13 ሚሊዮን ብርበማጭበርበር አውጥተው ሲያዘዋውሩ የነበሩ ተጠርጣሪ ግለሰቦችም መያዛቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ግርማይ ንጉሴ ተክላይ እና ያዘው ክበበው ወርዶፋ የተባሉ ተጠርጣሪ ግለሰቦች ገዛኢ አድሃኖም በእጣ በተባለ ግለሰብ ስም በተከፈተ የቁጠባ ሂሳብ ደብተር ውስጥ ከተቀመጠ 40 ሚሊዮን ብር መቀሌ የወጣመንጃ ፍቃድ ይዘው ጎላጎል አካባቢ ከሚገኘው አንበሳ ኢንርናሽናል ባንክ በመቅረብ 13 ሚሊየን ብር አውጥተው እዚያው ባንኩ ውስጥ በግርማይ ንጉሴ ተክላይ ስም በተከፈተ የባንክ ደብተር በማዘዋወር ላይእያሉ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡

እጅ ከፍንጅ ከተያዙት ተጥርጣሪ ግለሰቦቹ ጋርም የአንበሳ እና የአቢሲኒያ ባንክ ያልተፃፈባቸው ቼክቅጠሎች፣ልዩ ልዩ የባንክ ደብተሮች፣ ሶስት ኤቲ ኤሞች በኤግዚቢትነት መያዛቸውን አዲስ አበባ ፖሊስኮሚሽን አመልክቷል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በአሁኑ ወቅት በርካታ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር እያዋለና ሴራቸውን እያከሸፈ ያለው ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመቀናጀት መሆኑንም አስታውቋል፡፡