በማይጠብሪ ግንባር በጠላት ላይ ከባድ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ደረሰ

ነሀሴ 11/2013 (ዋልታ) – የ24ኛ ቴዎድሮስ ክፍለ ጦር በአሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን ላይ የማያዳግም እርምጃ እየወሰደ ነው፡፡
በዚህም ጦሩ በማይጠብሪ ግንባር በጠላት ላይ ከባድ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረሱን አስታውቋል፡፡
ክፍለ ጦሩ የተለያዩ መሣሪያዎችን ማርኳል  በአሁኑ ጊዜም የተበታተነውን የአሸባሪውን ቡድን አባላት በማደን እየደመሰሰ መሆኑን አመላክቷል ሲል አሚኮ ዘግቧል፡፡