በምግብ ራስን መቻል የክብራችን ማስጠበቂያ አንዱ መንገድ ነው- ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ነሃሴ 26/2013 (ዋልታ) – በምግብ ራስን መቻል የክብራችን ማስጠበቂያ አንዱ መንገድ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

በከተማችን የከተማ ግብርና ልምድ እንዲዳብር እና ከዘርፉ የሚገኘው ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር በርካታ ስራዎችን እያከናወንን እንገኛለን ያሉት ምክትል ከንቲባዋ በዚህም አበረታች ዉጤቶች ማስመዝገብ ጀምረናል ብለዋል።

በጓሮ አትክልት ልማት፣ በወተትና የወተት ተዋፅዖ፣ በዶሮና እንቁላል ልማት፣ በሰብል ምርት ላይ በጎ ጅምር መታየቱን የገለጹት ወይዘሮ አዳነች፣ በቀጣይ እንደ ከተማ ይበልጥ ውጤታማ መሆን እንደምንችል አመላክቷል ማለታቸውን ከከተማው ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያሳያል።