በሠመራ እና አንዳንድ የአፋር ክልል ከተሞች ላይ ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል ዳግም ጀመረ

ታኅሣሥ 12/2014 (ዋልታ) አሸባሪው የሕወሓት ቡድን በአፋር ክልል ወረራ ባደረገበት ወቅት የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ ውድመት በማድረሱ በክልሉ ከኮምቦልቻ ሰብስቴሽን የሚያገኙት 7 አገልግሎት መስጫ ማዕከላት መሉ በሙሉ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሳያገኙ መቆየታቸው ተገልጿል፡፡

ሆኖም የአፋር ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት አመራርና ሠራተኞች ባደረጉት ርብርብና የጥገና ሥራ ከትላንት ጀምሮ ሠመራ፣ ሎጊያ፣ ዱብቲ፣ አይሳኢታ፣ ሚሌ፣ ዲችኦቶ፣ ኤሊዳኣር እና ጋላፊ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል ዳግም አግኝተዋል፡፡

ኤሌክትሪክ በከተሞቹ የማገናኘቱ ሥራ የመዘግየቱ ምክንያት ከኮምቦልቻ ሰብስቴሽን ላይ የኃይል መዋዠቅ በማስከተሉና የኦፕቲካል ፋይበር ጥገና ባለመጠናቀቁ ምክንያት መሆኑን የአፋር ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡

በመሆኑም በከተሞቹ አልፎ አልፎ የኃይል መቆራረጥ ችግር ሊያጋጥም እንደሚችል መገለጹን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡